የቢሮው ስልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነት
ዘመናዊ፣ ፍትሐዊ እና ግፍጽ የገቢ አሰባሰብ ስርዓት ለአዲስ አበባ ብልጽግና
በአዋጅ ቁጥር 200/2023 መሠረት የተደነገጉ ዋና ዋና ተግባራት
ስልጣንና ተግባራት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ሕጋዊ የተፈቀደለት ዋና ዋና ተግባራት | Core mandates & responsibilities under Proclamation
ዘመናዊ የገቢ አወሳሰን ሥርዓት
ዘመናዊ የገቢ አወሳሰንና አሰባሰብ ስርዓት በመዘርጋት ተግባራዊ ማድረግ። ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ ሥርዓት በማስፋፋት ቅልጥፍናን ማረጋገጥ።
ፍትሐዊ አገልግሎት & ኢንቨስትመንት ማበረታቻ
ፍትሐዊ፣ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት። ለባለሀብቶች የተሰጡ የታክስ ነጻ መብቶች በሕግ መሠረት እንዲፈጸሙ ማድረግና መከታተል።
Investment-friendly complianceየግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች
ታክስ ከፋዮች በፈቃደኝነት ታክስ የመክፈል ባህልን እንዲያዳብሩ የግንዛቤ ፕሮግራሞችን ተግባራዊ ማድረግ። ማህበረሰቡን በታክስ ግዴታዎች ማስተማር።
ጥናትና ምርምር
የታክስ መመሪያዎችን አፈጻጸም ለማሻሻል እና ገቢ በአግባቡ እንዲሰበሰብ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ማካሄድ። መረጃ ተኮር ውሳኔዎችን ማጠናከር።
መረጃ ስብስብ፣ ትንተናና ስታቲስቲክስ
ለግብር አወሳሰን የሚያስፈልጉ መረጃዎችን መሰብሰብ፣ መተንተን፣ የተሟላ ስታትስቲክስ ማጠናቀር እና ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ።
የገቢ ውሳኔና ማሳወቂያ
በከተማ የሚሰበሰቡ ገቢዎችን ወስኖ ውሳኔዎችን ለግብር ከፋዮች በጽሁፍ ማሳወቅ፣ አሰራር ዘዴዎችን በመቀየር ቀልጣፋ ገቢ ማሰባሰብ።
ገቢ ለፋይናንስ ቢሮ ማፍሰስ
በተዋረድ ባቋ የቢሮው አደረጃጀት የሚሰበሰቡ ገቢዎች ለፋይናንስ ቢሮ በወቅቱ ፈሰስ ማድረግ። የግልጽነት አሠራርን ማረጋገጥ።
ደረሰኝ ማሳተምና የታክስ ህግ ማስከበር
ግብር ከፋዮች ደረሰኝ እንዲያሳትሙ መፍቀድ፣ መቆጣጠር እና አግባብ ባለው ህግ መሰረት የታክስ ህጎችን ማስከበር።
የቀን ገቢ ግምት ጥናት
አግባብ ባለው ህግ መሰረት የቀን ገቢ ግምት ጥናት ማከናወን። የገቢ ትንበያ እና ውጤታማ እቅድ ማውጣት።
አጋርነት እና የህብረተሰብ ተሳትፎ
አግባብነት ካላቸው አካላት እና የከተማ ነዋሪዎች ጋር በአጋርነት ለመስራት የሚያስችል ስልት በመቀየር ተግባራዊ ማድረግ።
የሰራተኞች አስተዳደር
የቢሮ ሰራተኞች ካቢኔው በሚያወጣው ደንብ መሰረት መቅጠር፣ ማስተዳደር እና ብቃት ያለው የሰው ሃይል መገንባት።
ሙያዊ እድገትህጋዊ ማዕቀፍ | Legal Framework
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አደረጃጀት አዋጅ ቁጥር 200/2023 እና ተያያዥ ደንቦች መሠረት የተሰጠውን ስልጣን በማክበር ዘላቂ የከተማ ልማት ገቢ ለማረጋገጥ ቁርጠኛ ነው።
Based on Proclamation No. 200/2023, the Bureau exercises its mandate to ensure fair tax administration,
digital transformation, and citizen-centric revenue mobilization.